የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ
ለውድ የፎረሙ አባሎች በሙሉ:-- ፎረሙን እንደምታዩት የተለያየ ማሻሻያዎች እያረግንበት ነው:: ይጨመር ይቀነስ የምትሉት ነገር ካለም: ለማስተካከል ዝግጁ ነን:: ጥያቄአችሁን ወይም ፓስት የምታደርጉትን ነገሮች በተሰጡት የካታጎሪ ምድቦች ውስጥ: እንደአይነቱ በአይነቱ እንድታስቀምጡ እያስታወቅን: Log in በማረግ ይጠቀሙ::
እናመሰግናለን፡፡ አድሚኖች::


ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስ እንሞክራለን:: በዚህ ፎረም ተረዳድተን ስለዲሽ: ሳተላይት ሪሲቨር: እንዲሁም ሪሲቨር ሶፍትዌሮች እንወያያለን::
 
HomeHome  CalendarCalendar  GalleryGallery  SearchSearch  RegisterRegister  Log in  

እንኩዋን ደህና መጡ
Who is online?
In total there are 2 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 2 Guests

None

Most users ever online was 41 on Sat Jul 02, 2016 11:21 am
Most active topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
Installers Phone Numbers And Location ዲሽ አስተካካዮች ስልክና አድራሻ እዚህ ያስቀምጡ
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Loader for all Spermax receivers
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Most Viewed Topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
በEutelsat 7E 12521 H 27500 የሚገቡ BISS channels
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
Loader for all Spermax receivers
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Top posting users this week
shambu
 

Share | 
 

 New** TV Varzish Channel on SD

Go down 
AuthorMessage
kstar
Senior member
avatar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

PostSubject: New** TV Varzish Channel on SD   Thu Jun 30, 2016 3:55 pm

የተለያዩ ታዳሚዎች varzish በSD ቻናላል ሆኖ በቢስ ኪ መጣ የሚለውን መረጃ ከተለያዩ ቦታዎች በመስማት ባላቸው የsd ሪሲቨር
ለማስገባት ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነቱን መምታታት ሊያስቀር ይችል ይሆናል በሚል አንድ ትምህርታዊ
ጽሁፍ አቅርበን ነበር(እዚህ ቢገቡ ጽሁፉን ያገኙታል )፡፡


ከዚህ ቀደም varzish በ11938H ላይ የሚያስተላልፈው ስርጭት ምንም እንኳን በተለምዶ HD ሪሲቨር የሚባለው ላይ ቢሆንም
የሚሰራው፤ ስርጭቱ ግን በርግጥ HD አልነበረም፡፡ ስርጭቱ በተለምዶ HD የሚባሉትን ሪሲቨሮች የፈለገበት ምክንያቱ እነዚህ ሪሲቨሮች MPEG4ን
ዲኮድ ማድረግ ስለሚችሉ ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም ግን SD ሪሲቨርም ሆኖ MPEG4 ዲኮድ ማድረግ እስከቻለ ድረስ ከላይ ባለው ትራንስፖንደር ላይ
የሚሰራጨውን በSD ሪሲቨሮች ላይም ማየት ይቻላል፡፡

varzish አሁን በሌላ ትራንስፖንደር ላይ ስርጭት ከፍቷል በ12015H ላይ፡፡ ይህኛው ስርጭት ከበፊቱ ለየት የሚያደርገው ኢንኮዲንጉ
MPEG2 በመሆኑ ነው፡፡ ያው እንደበፊተኛው ሁሉ ይህኛውም HD አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ስርጭት የሚያስተላልፈው ትራንስፖንደር
ስርጭቱን የሚለቀው በDVBS-2 ስታንዳርድ ነው፡፡ ያማለት ደግሞ አብዛኞቹ በየቤታችን የሚገኙት የSD ሪሲቨሮች ኢምፕሊመንት ያደርጉት
የDVB-Sን ስታንዳርድ ስለሆነ የDVB-S2 ስታንዳርድን የሚጠቀሙ ስርጭቶችን ሊያሳዩን አይችሉም፡፡ በነዚህ DVB-S ሪሲቨሮች ላይ የዚህን
ትራንስፖንደር ሲግናል እንኳን አክቲቭ አድርገው ሊያሳዩን አይችሉም፡፡ ምናልባት ይህ ሲሆን የዲሽ ሳህኑ ሳይስተካከል ቀርቶ መስሏችሁ በደምብ
አስተካክይ ሲግናል ኳሊቲዉን ብጨምረው ይገባልኛል በሚል ተስፋ ስትደክሙ እንዳትዉሉ!!

ችግሩ ያለው DVB-S2 ስታንዳርድ ባክዋርድ ኮምፓተብል ሆኖ ስላልተሰራ የDVB-S ሪሲቨሮች ሲግናሉን እንኳን እንደ ማንኛውም ኖይዝ
(noise) ነው የሚቆጥሩት፣ ማለትም 'ሲግናል ሎክ' ሊያደርጉት አይችሉም፤ ሪኮግናይዝ ስለማያደርጉት፡፡

ይህም ማለት ምንም እንኳን varish በዚህ በአዲሱ ስርጭቱ ላይ ኢንኮዲንጉን ወደ MPEG2 ቢቀይርም እንኳን እንደውም የበፊቱ ላይ
ይሰሩ የነበሩ በርካታ DVB-Sን ብቻ ኢምፕሊመንት ያደረጉ የHD ሪሲቨሮች ይህኛው ላይ ሲግናል እንኳን አያመጡላችሁም፡፡
በአብዛኛው ቤት በሚገኙት የSD ሪሲቨሮች መመልከት የሚቻለው ኢንኮዲንጉን ብቻ ሳይሆን ስታንዳርዱንም በDVB-S አድርጎ ማሰራጭት
ከጀመረ ብቻ ነው፡፡ አሁን የሆነው ግን ያ አይደለም፡፡

በነገራችን ላይ ይህ ትራንስፖንደር 12015H ከጥቂት ወራት በፊት የሚያሰራጨው በDVB-S ስታንዳርድ ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ግን
ስርጭቱን ወደ DVB-S2 ቀይሮታል፡፡

ከላይ ያለው ገለጻ ትንሽ ቴክኒካል ከሆነባችሁ፤ በየቤታችን የሚገኙት የSD ሪሲቨሮች አሁን የመጣውን varish ሊያሳዩን አይችሉም የሚለውን
ማጠንጠኛ ከያዛችሁ ይበቃል፡፡ ያው የተቀረው የዚህ ጽሁፍ አካል 'ለምን? እንዴት?' ብለው ማወቅ የፈለጉትን ለማስረዳት በማሰብ የተደረግ
መጠነኛ ገለጻ ነው፡፡ ይህ መረጃ ጠቃሚ ነበር ብለው ካሰቡ በስተቀኝ የሚታየውን የ ፕላስ(+) ምልክት ይጫኑ፡፡

ኢትዮዲሽ ፎረም ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ታማኝና ሳይንሳዊ የሆነ መረጃን ለታዳሚዎቹ ሃላፊነት በተሞላበት መልኩ ማቅርቡን ይቀጥላል፡፡


⛔ይህን መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ➕ ጫን ያርጉ፡፡


Last edited by kstar on Thu Jul 07, 2016 10:56 am; edited 1 time in total
Back to top Go down
kstar
Senior member
avatar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Thu Jun 30, 2016 8:33 pm

ይህ TP የስርጭት ስታንዳርዱን አሁን ካለበት የDVB-S2 ትራንስሚሽን ቀይሮ ቀድሞ ሲያሰራጭ በነበረበት በDVB-S ማሰራጨት ከጀመረ፤
በዚሁ ፎረም ላይ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
ሌሎችም ታዳሚዎች ለውጥ ካያችሁ እዚሁ መልዕክት በማስቀመጥ ወቅታዊ መረጃን ለብዙሃን ማጋራትን አትርሱ፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
avatar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Sun Jul 03, 2016 12:12 pm

..
Back to top Go down
mmm3
Member


Posts : 46
Points : 60
Reputation : 12
Join date : 2014-10-06

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Tue Jul 05, 2016 9:43 am

በsuper max2425
Back to top Go down
mmm3
Member


Posts : 46
Points : 60
Reputation : 12
Join date : 2014-10-06

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Tue Jul 05, 2016 9:45 am

በsuper max 2425 HD varzish sd ተከፍቷል/አልተከፈተም?
Back to top Go down
mulukenararsa89
Member


Posts : 173
Points : 247
Reputation : 54
Join date : 2015-10-03
Age : 32
Location : Aleta chuko

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Tue Jul 05, 2016 4:12 pm

mmm3 esikeahun alitekefetem be ibox gn enidemigeba negirewugnal be 2425 HD misera kehone ezihu forum lay post yideregal
Back to top Go down
natinani17Posts : 6
Points : 8
Reputation : 2
Join date : 2016-06-01

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Thu Jul 07, 2016 5:54 pm

hello k star kezi befit endenegerkegn varzish hd be 12015 xx ምልክት aderegehebet beamu egna ga endemayderse new ena ahun sd hono be biss key ketejemere buhala endet new teret belo megebat yehechelal weye ? ket ket eyale yaschegeral neger menem enkua belelachaw ferequency varshi hd m refardanem mastekakel bechelm. be 12015 still ket ket n track neger alew ur response is highly appreciated.
Back to top Go down
kstar
Senior member
avatar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   Thu Jul 07, 2016 8:00 pm

natinani17 wrote:
hello k star kezi befit endenegerkegn varzish hd be 12015 xx ምልክት aderegehebet beamu egna ga endemayderse new ena ahun sd hono be biss key ketejemere buhala endet new teret belo megebat yehechelal weye ? ket ket eyale yaschegeral neger menem enkua belelachaw ferequency varshi hd m refardanem mastekakel bechelm. be 12015 still ket ket n track neger alew ur response is highly appreciated.

ትክክል ነው፡፡ ያንን ባልኩበት ወቅት የነበረው የሲግናል ሌቭል እኛ ጋር በቂ አልነበረም፡፡
እንደሚታወቀው የሳታላይት ካምፓኒዎች የአንድን ትራንስፖንደር ፖወር ሌቭል በፈለጉበት ግዜ ሊጨምሩት ወይም ሊቀንሱት ይችላሉ፡፡
አሁን ላይ ባለው የሲግናል ሌቭል እኛ ጋር ለመመልከት ይቻላል፤ ሆኖም በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍሎች ላይ ተለቅ ያለ ሳህን ያስፈልገዋል፡፡
አሁን ግዜው ክረምት እንደመሆኑ ከሌሎች በተለየ ሁኔታ እዚህ ላይ ያለው በቀላሉ የመታወክ ባህሪም አለው፡፡
ለዚህም ይመስላል ብዙ ተጠቃሚዎች አንስቴብል እንደሆነባቸው ነው የሚናገሩት፡፡

ከዚህ በተረፈ ምናልባት ከላይ ለማሳሰብ እንደሞከርኩት የትራንስሚሽን ስታንዳርዱን ቀይረው በDVB-S ማሳየት ከጀመሩና በማንኛውም
SD ሪሲቨር ላይ መስራት መጀመሩን ካረጋገጥክ እዚሁ ፎረም ላይ መጠህ አፕዴት ብታደርገን በጣም ጥሩ ይሆናል፡፡ ያው እኛ ሁሉንም መረጃ
በየቀኑ ሞክረን ለማረጋገጥ የጊዜ አለመመጣጠን ሊኖር ስለሚችል ሌሎች የፎረሙ አባላትም በስራ ውይም በሌላ ጉዳይ ያገኛችሁትን
የተረጋገጠ መረጃ ለሌሎች በማካፈል መረጃውን ወቅታዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

/ኢትዮዲሽ ፎረም
Back to top Go down
Sponsored content
PostSubject: Re: New** TV Varzish Channel on SD   

Back to top Go down
 
New** TV Varzish Channel on SD
Back to top 
Page 1 of 1
 Similar topics
-
» Channel 4 Thursday 1st April Lost Abroad - The Parents Story
» Was the Real Purpose of Channel 4 Dispatches 'Searching For Madeleine' to Discredit the PJ?
» Dispatches - The Real Mr & Mrs Assad - Channel 4
» Benefit Street: Channel 4
» Teamspeak 3 - Channel Hotkeys

Permissions in this forum:You cannot reply to topics in this forum
የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ :: Encryption / Decryption :: Frequency-
Jump to: