የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ
ለውድ የፎረሙ አባሎች በሙሉ:-- ፎረሙን እንደምታዩት የተለያየ ማሻሻያዎች እያረግንበት ነው:: ይጨመር ይቀነስ የምትሉት ነገር ካለም: ለማስተካከል ዝግጁ ነን:: ጥያቄአችሁን ወይም ፓስት የምታደርጉትን ነገሮች በተሰጡት የካታጎሪ ምድቦች ውስጥ: እንደአይነቱ በአይነቱ እንድታስቀምጡ እያስታወቅን: Log in በማረግ ይጠቀሙ::
እናመሰግናለን፡፡ አድሚኖች::


ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስ እንሞክራለን:: በዚህ ፎረም ተረዳድተን ስለዲሽ: ሳተላይት ሪሲቨር: እንዲሁም ሪሲቨር ሶፍትዌሮች እንወያያለን::
 
HomeHome  CalendarCalendar  GalleryGallery  SearchSearch  RegisterRegister  Log in  

እንኩዋን ደህና መጡ
Who is online?
In total there is 1 user online :: 0 Registered, 0 Hidden and 1 Guest :: 1 Bot

None

Most users ever online was 41 on Sat Jul 02, 2016 11:21 am
Most active topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
Installers Phone Numbers And Location ዲሽ አስተካካዮች ስልክና አድራሻ እዚህ ያስቀምጡ
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Loader for all Spermax receivers
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Most Viewed Topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
በEutelsat 7E 12521 H 27500 የሚገቡ BISS channels
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
Loader for all Spermax receivers
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Top posting users this week

Share | 
 

 ስለ BeIN Sport ጥቂት መረጃ

Go down 
AuthorMessage
Admin
Admin
avatar

Posts : 727
Points : 1176
Reputation : 304
Join date : 2014-09-01

PostSubject: ስለ BeIN Sport ጥቂት መረጃ   Sat Nov 07, 2015 9:44 am

ስለ BeIN Sport ጥቂት መረጃ ጀባ ልበላችሁ::

ሁላችንም እንደምናውቀው BeIN Media Group በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ አካባቢዎች (አሁን በሩቅ ምሥራቅ በካናዳም ያሰራጫል) እግር ኳስን ከ2013 ጀምሮ በከፍተኛ ጥራት በሳተላይት የሚያሰራጭ ካምፓኒ ነው:: በእዚህም አገልግሎቱም እስካሁን ወደ10 ሚሊዮን የሚጠጉ የBeIN Sport ካርድ የገዙ አባላት አሉት::

ይህ ካምፓኒ አሁን አነዚህን ካርድ የገዙ አባሎቹን ለማሳደግ ስትሪተጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው:: እስከዛሬ ካርዱን የገዙ ደንበኞቹ ኳስ የሚወዱ ብቻ ነበሩ ምክንያቱም ኳስ ብቻ ስለሚያስተላልፉ:: ይህንን የአባሎቹን ቁጥር ለማሳደግ የቀየሰው ዘዴ ደግሞ ሌሎች ኳስ ብዙም የማይወዱ ነገር ግን ጥናታዊ የሆኑ: የመዝናኛ ፊልሞችን: ትምህራታዊ የሆኑ ፊልሞች: እና የህፃናት ቻናሎችን ቢጨምር: ተጨማሪ ደንበኞች ሊያገኙ እንደሚችሉ አቀዱ:: ስለዚህ መጀመርያ የወሰዱት እርምጃ ዲጂተርክን መግዛት ነው:: አሁን ዲጂተርክን ገዝተው የቀራቸው ትንሽ የወረቀት ሥራ ብቻ ነው:: እሱንም በእዚህ አንድ ወር ውስጥ ይጨርሱታል ተብሎ ይገመታል::

ስለዚህ እስከአሁን በኳስ ላይ ብቻ አተኩሮ የነበረው ፕሮግራማቸው አሁን የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመጨመርና ለደንበኞቻቸው በማቅረብ እስካሁን የነበሩ የደንበኞቻቸውን ብዛት በእጥፍ ለማሳደግ ቆርጠው ተነስተዋል::

እንደሚታወቀው ወደፊት እነሱም በእኛ ሃገር ላይ ትኩረት አድርገው: ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው: እስከሚገቡ ድረስ አሁን ምንም እንኳ ስርጭታቸው እኛ ሃገር ቢደርስም የእነሱን አገልግሎት መጠቀም ሕገወጥ ነው:: ከእዚህ በፊት በማስ ሚድያ እንደሰማነው: በኢትዮጵያ ውስጥ የBeIN Sport ካርድ መጠቀም ያስቀጣል:: ይህ ብቻ ሳይሆን ራሱም Bein Media ካምፓኒ: ካርዳቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምንጠቀም ካወቁ ካርዱን Block ያደርጉታል::

ይህ እንዳለ ሆኖ ለግንዛቤ ያህል ከትላንት (01-11-2015) ጀምሮ የተለያዩ ፓኬጆችን በተለያዩ ዋጋ አቅርበዋል እነሱም እነዚህ ናቸው::

1. Access Package
ይህ ፓኬጅ የያዘው ቻናሎች
አራት የኤሮፕ የኳስ ግጥሚያና ሌሎች ስፖርቶችን የሚያሳዩ ቻናሎች (England, Spain, German, France, Italy, etc...)
BeIN Sport 7/8/9/10
አራት የመካከለኛው ምሥራቅ የኳስ ግጥሚያ የሚያሳዩ ቻናሎች (Middle East football games)
Alkass 5/6/7/8
ሶስት የፊልምና አንድ የዘፈን ቻናሎች
Fox Movies HD - Fox HD - Star World HD - V HD
ሁለት ጥናታዊና አንድ የልጆች ቻናሎች
National Geography People HD - National Geography Wild HD
Baby TV HD
እነዚህን 14 ቻናሎች ለማግኘት ለAccess Card በወር (Monthly) የሚከፈለው 10.00 ዶላር ወይም 213.00 ብር ነው

2. Top Movies package
ይህ ፓኬጅ የያዘው ቻናሎች ደግሞ በAccess ፓኬጅ ያሉት እንዳሉ ሆነው በተጨማሪ 4 ቻናሎች አሉት
ሁለት አዳዲስ ፊልሞችን የሚያሳዩ ቻናሎች
BeIN Movies 1&2
አንድ የፊልም ቻናል - Star Movies HD
አንድ ጥናታዊ ቻናል - National Geography HD
እነዚህን 18 ቻናሎች ለማግኘት ለTop Movies Card በወር (Monthly) የሚከፈለው 25.00 ዶላር ወይም 533.00 ብር ነው

3. Top Sports Package
ይህ ፓኬጅ የያዘው ቻናሎች ደግሞ በAccess ፓኬጅ ያሉት እንዳሉ ሆነው በተጨማሪ 13 የኳስና አንድ የባስኬት ቻናሎች አሉት
አስራ ሶስት የስፖርት ግጥሚያ የሚያሳዩ ቻናሎች
BeIn Sports 1/2/3/4/5/6/11/12/13/14/15/16/17
አንድ የባስኬት ቦል ግጥሚያ የሚያሳይ ቻናል - NBA channel
እነዚህን 28 ቻናሎች ለማግኘት ለTop Sports Card በወር (Monthly) የሚከፈለው 25.00 ዶላር ወይም 533.00 ብር ነው::

4. Complete Package
ይህ ፓኬጅ የያዘው ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን 3 ፓኬጆችን በሙሉ አጠቃሎ የያዘ ነው::
ይሄንን Complete Package ለማግኘት ደግሞ በወር (Monthly) የሚከፈለው 30.00 ዶላር ወይም 640.00 ብር ነው

5. ለእዚህ አመት ደግሞ ተጨማሪ ፓኬጅ አላቸው Euro 2016 ውድድር ለማየት ለእሱም ተጨማሪ 4 ቻናሎችን BeIn Max 1/2/3/4 የሚል ጨምረዋል::

ይህንን የይሮ 2016 ውድድር ለማየት ተጨማሪ 60.00 ዶላር ወይም 1276.00 ብር ያስከፍላሉ::
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ቻናሎች ለማግኘት ሁለት ሳተላይቶችን መጠቀም ይቻላል
አንደኛው Eutelsat 25B / Es'hail-1 @ 25.5° East (በዘልማድ አረብሳት 26E በምንለው) ፍሪኪዌንሲዎቹን ለማግኘት ይሄንን ሊንክ ይጠቀሙ::

[You must be registered and logged in to see this link.]

ሁለተኛው ደግሞ በናይልሳት 7w ነው:: ፍሪኪዌንሲዎቹን ለማግኘት ይሄንን ሊንክ ይጠቀሙ::

[You must be registered and logged in to see this link.]
Back to top Go down
http://ethiodish.amharicforum.com
 
ስለ BeIN Sport ጥቂት መረጃ
Back to top 
Page 1 of 1
 Similar topics
-
» How Kenya Sport Officials are abetting Illegal Travel............
» What is the Capital of Israel?

Permissions in this forum:You cannot reply to topics in this forum
የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ :: Encryption / Decryption :: General Discussions: Encryption / Decryption-
Jump to: