የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ
ለውድ የፎረሙ አባሎች በሙሉ:-- ፎረሙን እንደምታዩት የተለያየ ማሻሻያዎች እያረግንበት ነው:: ይጨመር ይቀነስ የምትሉት ነገር ካለም: ለማስተካከል ዝግጁ ነን:: ጥያቄአችሁን ወይም ፓስት የምታደርጉትን ነገሮች በተሰጡት የካታጎሪ ምድቦች ውስጥ: እንደአይነቱ በአይነቱ እንድታስቀምጡ እያስታወቅን: Log in በማረግ ይጠቀሙ::
እናመሰግናለን፡፡ አድሚኖች::


ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስ እንሞክራለን:: በዚህ ፎረም ተረዳድተን ስለዲሽ: ሳተላይት ሪሲቨር: እንዲሁም ሪሲቨር ሶፍትዌሮች እንወያያለን::
 
HomeHome  CalendarCalendar  GalleryGallery  SearchSearch  RegisterRegister  Log in  

እንኩዋን ደህና መጡ
Who is online?
In total there is 1 user online :: 0 Registered, 0 Hidden and 1 Guest :: 1 Bot

None

Most users ever online was 41 on Sat Jul 02, 2016 11:21 am
Most active topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
Installers Phone Numbers And Location ዲሽ አስተካካዮች ስልክና አድራሻ እዚህ ያስቀምጡ
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Loader for all Spermax receivers
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Most Viewed Topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
በEutelsat 7E 12521 H 27500 የሚገቡ BISS channels
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
Loader for all Spermax receivers
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Top posting users this week

Share | 
 

 እንዴት ነው በየቤታችን በሳተላይት የተላኩ የቲቪ ፕሮግራሞችን የምናየው??

Go down 
AuthorMessage
Admin
Admin
avatar

Posts : 727
Points : 1176
Reputation : 304
Join date : 2014-09-01

PostSubject: እንዴት ነው በየቤታችን በሳተላይት የተላኩ የቲቪ ፕሮግራሞችን የምናየው??   Fri Aug 28, 2015 4:53 pm

እንዴት ነው በየቤታችን በሳተላይት የተላኩ የቲቪ ፕሮግራሞችን የምናየው??

የቲቪ ካምፓኒዎች ፕሮግራሞቻቸውን ወደ ሳተላይት የሚልኩበት መንገድ አፕሊንኪንግ (up-linking) ሲባል: ከሳተላይት ደግሞ ወደእኛ የሚመጣው ዳውንሊንኪንግ (down-linking) ይባላል::
በመጀመርያው DTH (Direct to Home) satellite TV የተጀመረው በዲሰምበር 1982 በተላከችው በAstra-1 ሳተላይት ሲሆን: ይህም የሳተላይትን ቲቪ አብዮትን አስጀምርዋል:: እንግዲህ ከላይ በጠቀስኩላችሁ መሠረት የቲቪ ካምፓኒዎች ፕሮግራሞቻቸውን ወደሳተላይቱ አፕሊንክ ሲያደርጉ: እኛ ደግሞ በየቤቶቻችን ይህንን ፕሮግራም ከሳተላይቱ ዳውንሊንክ ለማድረግ ጣራ ላይ በሰቀልነው ዲሽና ኤልኤንቢ አማካኝነት: ከእዛም በኬብል: ቀጥሎም ሳተላይት ሪሲቨር ቦክስ ወይም ዲኮደር: ከእዛም ከቴሌቭዢኖቻችን ጋር በማያያዝ ምስሎቹን እንመለከታለን::
ይህንን ሂደት በአጭሩ ለማስቀመጥ...

ቲቪ ካምፓኒዎች ፕሮግራሞቻቸውን ማለትም ቪዲዮቻቸውን ወደሳተላይቱ ለመላክ ቪዲዮቻቸውን ባነሱበት ፎርማት አይነት ወደሳተላይቱ አይልኩትም:: ምክንያቱም ዳታው በጣም ትልቅ ስለሚሆን: ከፍጥነት አንፃር: ከወጪ አንፃር: ዳታ ከመጥፋት: ወይም ከመባከን አንፃር: በነበረት አይነት ፎርማት አይልኩትም:: የሚልኩት በጣም በታመቀ (compressed) በሆነ አነስተኛ የዳታ አይነት ነው::
(ይህንን የአላላክ ዘዴ ስለMPEG2 እና MPEG4 በማስረዳበት ጊዜ ይበልጥ እተነትነዋለሁ)
ከእዛም ከሳተላይቱ (ከመሬት እስከ 36000ኪሜ ይርቃል) ወደየቤታችን ጣራ ላይ ወደተሰቀለው ዲሽ በራዲዮ ማግኔቲክ ዌቭ ወይም ማክሮዌቭ (radio electromagnetic waves or Microwaves) በትልቅ ፍሬክዌንሲ 10-13 ጊጋ ሄርዝ በሚደርስ ይመጣል:: በእዚህ ትልቅ የራዲዮ ማግኔቲክ ዊቭ ፍርክዌንሲ መምጣቱ ረጅም ርቀት ምንም አይነት የዳታ መባከን ሳያጋጥመው በፍጥነት እንዲጓዝ ይረዳዋል:: ነገርግን እነዚህ በትልቅ ፍጥነትና ሃይል የሚመጣው ሞገድ: ጠጣር ነገሮችን: ማለትም ግርግዳዎችን እና የመሳሰሉትን ማለፍ አይችልም:: ስለዚህ ጣራ ላይ ወይም ከፍ ያለ ቦታ የሰቀልነው ዲሽ ይህንን በከፍተኛ ፍጥነት ከሳተላይት የሚመጣ ሞገድ ለመቀበል ምንም አይነት የሚከልለው ነገር መኖር የለበትም:: የዲሹም አቅጣጫ ቀጥታ ወደሳተላይቱ መሆን አለበት:: ሳህኑ ላይ ያረፈው ከሳተላይት የመጣው ሞገድ ነጥሮ ወደ ኤልኤንቢው LNB ይሄዳል:: ይህ LNB በትልቅ ፍሪኪዌንሲ የመጣውን ሞገድ በመጣበት ፍሪኪዎንሲ ወደ ሪሲቨራችን በኬብል አማካኝነት ቢሄድ: በጣም ብዙ የሆነ የዳታ ብክለት ስለሚኖር: ይሄን ለማስቀረት በትልቅ ፍሪኬውንሲ የመጣውን ወደ ትንሽ ፍሪኪዌንሲ (ከ2 ጊጋ ሄርዝ ወዳነሰ) ይለውጠዋል::

ከእዛ ዳታው ወደሪሲቨራችን ይመጣል:: በሪሴቨራችንም በኬብል አማካኝነት ምስሉን በቲቪያችን እናየዋለን::

ከሳተላይት የመጣውን የምስል ዳታ እንዴት ነው የምናየው???

የቲቪ ምስል በአቬሬጅ 25 ፍሬም በሰከንድ ነው ያለው እንደ ፓል (PAL) አይነት ሲስተም ሲሆን:: እንደ ኤንቲኤስሲ (NTSC) አይነት ሲሆን ደግሞ 30 ፍሬም በሰከንድ ነው ያለው:: እያንዳንዱ ፍሬም የማይንቀሳቀስ አንድ አንድ ምስል ነው ያለበት:: እነዚህ አንድ አንድ የማይንቀሳቀሱ ፍሬሞች በአንድ ሰከንድ ውስጥ በፍጥነት ሲንቀሳቀሱ እንቅስቃሴ ያለው ፊልም ማየት እንችላለን:: ከእዛ ባለፈ ለእዚህ እንዲረዳ እንደ ቴሊቪዥኑ አይነት ሪዞሉሽን የሚባል ነገር አለ:: ለምሳሌ የዱሮ ቴሌቭዢን 480 መስመሮች (480 lines) ሲኖሩት: ኤች ዲ ሬዲ (HD Ready) ወይም ዲቪዲ የሆኑ ደግሞ 720 መስመር (720 lines) አላቸው:: ኤች ዲ ቲቪ (HDTV) እና ብሉ ሬይ ዲቪድ (Blu-Ray DVD players) ደግሞ 1080 መስመር (1080 lines) አላቸው:: የመስመሮቹ ወይም የላይኖቹ መብዛት የምናየውን ምስል በጥራት እንድናየው ያደርጋል::

የቲቪ ካምፓኒዎቹ ባንድዊዙን ለመቀነስ (ባንድዊዝ ማለት በየሰከንድ የሚተላለፈው ዳታ ማለት ነው) በየሰከንዱ የሚሰራጨውን ፍሬም ሁለት ቦታ ይከፍሉታል:: ኦድ መስመር (odd lines) የሆኑትን 1 3 5 7 ወዘተ... አንድ ፍሬም ላይ: ኢቭን መስመር (even lines) የሆኑትን 2 4 6 8 ወዘተ... ሁለተኛ ፍሬም ያደርጉታል:: የተከፈለውን አንዱን ፍሬም: ይህ ማለት ከላይ በሰከንድ 25 ፍሬም ያልነው አሁን በሰከንድ 50 ፍሬም ይሆናል ሲከፍሉት::

ከላይ ቲቪ ካምፓኒዎች ፕሮግራማቸውን መጀመርያ በሰሩበት ፎርማት እንደማይልኩና በጣም አሳንሰው እንደሚልኩ ነግሪያችሁ ነበር:: አንድ የቲቪ ፒክቸር ሁለት ቦታ ሲከፍሉት በሰከንድ 50 ፍሬም እንደሚኖረውም ከላይ ነግሪያቸሁዋለ::

ለምሳሌ አንድ ሰው ቆሞ እጁን ወደላይ የሚያነሳ ፊልም ብናይ ... የመጀመርያው 50 ፍሬም በሰከንድ የሚታየው ሰውየው ቆሞ እናየዋለን:: እጁንም ታች እንዳለ እናየዋለን:: በሚቀጥለው ሰከንድ ደግሞ እጁ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ብናይ በ50ው ፍሬሞች በሰከንድ ውስጥ በሚያልፈው እጁ ቀስ በቀስ ከፍ ያለ ምስል ነው በፍጥነት የሚያልፈው::

የቲቪ ካምፓኒዎቹ የሚያወጡትን ወጪ ለመቀነስ ይህ አሁን የተጠቀምንበትን ምሳሌ ብንወስድ በሰከንድ ውስጥ የሚያልፉትን 50 ፍሬሞች ለሁለት ይከፍሉታል:: አንደኛው ፍሬም (ኦድ መስመር (odd lines) የሆኑትን 1 3 5 7 ወዘተ... የያዘው: የማይንቀሳቀሰውን የሰውየው ሰውነት የሚያሳይ ሲሆን: ሁለተኛው ደግሞ (ኢቭን መስመር (even lines) የሆኑትን 2 4 6 8 ወዘተ... ) የሚንቀሳቀሰውን የሰውየው እጅ ብቻ የያዘ ፍሬም ይሆናል:: ስለዚህ የማይንቀሳቀሰው የሰውየውን ዳታ የያዘ ፍሬሞች አንዴ ብቻ ይልኩና: የሚንቀሳቀሰውን የሰውየው እጅ ደግሞ በተከታታይ ባሉ ሰከንዶች ይልካሉ:: ይህ በአንዴ ብዙ ዳታ ከመላክ ይታደጋቸዋል:: ይህንን አንድ ምሳሌ በብዙ አብዝተን ስናየው: በጣም ብዙ ዳታ ከመላክ ይገላግላቸዋል:: ይህም ብዙ ወጪ ይቀንስላቸዋል:: እነዚህ በተለያየ ሁኔታ ተከፍለው የተላኩ ሲግናል ፍሬሞች ዲኮደራችን እየገጠመ በስርአት እኛ እንድናይ ይረዳናል:: ይህ ቲቪ ካምፓኒዎቹ ወጪን ለመቀነስ የሚጠቀሙበት ዘዴ ቪድዮ ኮምፕሬሽን (Video compression technology) ይባላል::

የታወቁት የቪድዮ ኮምፕሬሽን ቴክኖሎጂዎች MPEG2 እና MPEG4 ይባላሉ::

MPEG2 እና MPEG4 ምንድነው ልዩነታቸው ምንድነው የትኛውስ ይሻላል??

ይህን ደግሞ ወደፊት በማቀርበው ፅሁፌ አብራራዋለሁ::

[img][You must be registered and logged in to see this image.][/img]
Back to top Go down
http://ethiodish.amharicforum.com
Kaleab470
Member


Posts : 102
Points : 119
Reputation : 11
Join date : 2015-06-21

PostSubject: Re: እንዴት ነው በየቤታችን በሳተላይት የተላኩ የቲቪ ፕሮግራሞችን የምናየው??   Sat Aug 29, 2015 12:48 pm

Thank you, Sami
Back to top Go down
 
እንዴት ነው በየቤታችን በሳተላይት የተላኩ የቲቪ ፕሮግራሞችን የምናየው??
Back to top 
Page 1 of 1

Permissions in this forum:You cannot reply to topics in this forum
የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ :: Installation and Support :: General Discussions: Installation and Support-
Jump to: