የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ
ለውድ የፎረሙ አባሎች በሙሉ:-- ፎረሙን እንደምታዩት የተለያየ ማሻሻያዎች እያረግንበት ነው:: ይጨመር ይቀነስ የምትሉት ነገር ካለም: ለማስተካከል ዝግጁ ነን:: ጥያቄአችሁን ወይም ፓስት የምታደርጉትን ነገሮች በተሰጡት የካታጎሪ ምድቦች ውስጥ: እንደአይነቱ በአይነቱ እንድታስቀምጡ እያስታወቅን: Log in በማረግ ይጠቀሙ::
እናመሰግናለን፡፡ አድሚኖች::


ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስ እንሞክራለን:: በዚህ ፎረም ተረዳድተን ስለዲሽ: ሳተላይት ሪሲቨር: እንዲሁም ሪሲቨር ሶፍትዌሮች እንወያያለን::
 
HomeHome  CalendarCalendar  GalleryGallery  SearchSearch  RegisterRegister  Log in  

እንኩዋን ደህና መጡ
Who is online?
In total there are 3 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 3 Guests

None

Most users ever online was 41 on Sat Jul 02, 2016 11:21 am
Most active topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
Installers Phone Numbers And Location ዲሽ አስተካካዮች ስልክና አድራሻ እዚህ ያስቀምጡ
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Loader for all Spermax receivers
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Most Viewed Topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
በEutelsat 7E 12521 H 27500 የሚገቡ BISS channels
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
Loader for all Spermax receivers
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Top posting users this week

Share
 

  የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች

Go down 
AuthorMessage
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyFri Aug 21, 2015 11:56 am

አስራምስተኛዉ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ....መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት ---------------->------------------->እዚጋ የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት------------->

አስራ አምስተኛው የአለም አትሌትክስ ሻምፕዮና ዛሬ አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ምሽት በድምቀት ይጀመራል፡፡
ውድድሩ ለቀጣዮቹ ዘጠኝ ቀናት ይቀጥላል፡፡
በዚህም ፎርም ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸውን ውድድሮች እና የውድድሩ ሰአቶች እንደዚሁም ውድድሩ የሚታይባቸውን ቻናሎች ዝርዝር ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
በነገራችን ላይ ይህ ዉድድር በብዙ FTA ቻናሎች ስለሚተላለፍ የውድድሩን ሰአት ማወቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ይሆናል፡፡

ከመክፈቻው ስነስረአት ቀድሞ አንድ የፍፃሜ ዉድድር ይካሄዳል፡፡ የወንዶች ማራቶን!
ኢትዮጵያ በዚህ ዉድድር በ ለሊሳ ደሲሳ ብርሀኑ ለሚ እና የማነ ፀጋይ ትሳተፋለች፡፡
ለሊሳ በዚህ አመት 2፡05፡52 የሆነ ሰአት አስመዝግቧል ፐርሰናል ቤስት ይሚባለው እና እስካሁን ከገባባቸው ሰአቶች ሁሉ ምርጡ ደግሞ 2፡04፡05 ነው፡፡
ብርሀኑ በዚህ አመት 2፡05፡28 የሆነ ሰአት አስመዝግቧል፡፡ ይህ ለራሱም ፐርሰናል ቤስት ተብሎ ተመዝግቦለታል፡፡
የየማነ በዚህ አመት ያስመዘገበው ምርጥ ሰአት በIAAF መዝገብ ላይ ባይሰፍርም አትሌቱ 2፡04:48 ፐርሰናል ቤስት እንዳለው ያሳያል፡፡
የውድድሩን መስፈርት አሟልተው ከቀረቡት ስልሳስምንት አትሌቶች ዉስጥ በፐርሰናል ቤስት ኬኒያውያኑ ላይ የሚደርስ አልተገኘም፡፡
ሁለት የኬኒያ ሯጮች 2፡02:57 እና 2፡03፡23 ፐርሰናል ቤስት ሰአት አስመዝግበዋል፡፡
በሲዝን ቤስት ደግሞ የኬኒያው አትሌት ኪፕሮቺ በ 2፡04፡47 ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መሃል ምርጡን የአመቱን ሰአት አስመዝግቧል፡፡
ብርሀኑ በ2፡05፡28 ከተወዳዳሪዎቹ መሀል ሁለተኛ ፈጣን ሰአት ይዟል፡፡
ባህሬን በ ሹሜ ደቻሳ፤ ስዊዘርላንድ ደግሞ በ ታደሰ አብርሐም ይሳተፋሉ፡፡
የዩጋንዳው ስቴፈን ኪፕሮቺም ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች ዉስጥ ይመደባል 2፡06፡33 አለው በዚህ አመት፡፡ ይህ ለሱ ፐርሰናል ቤስትም ጭምር ነው፡፡
እንግዴ ስለ አትሌቶቻችን ይህን ያክል ካልኩ ስለ ዉድድሩ ሰአት ልንገራችሁና አብረን በቴሌቪዝን መስኮት እንከታተል፡፡
ይህ የማራቶን ዉድድሩ አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ከምሽቱ በስምንት ሰአት ከሰላስ አምስት (ምሽት 8:35) ላይ ይካሄዳል፡፡
ዉድድሩ ወደ ሁለት ሰአት ስለሚቆይ ሌሊት አስር ሰአት ብቅ ብላችሁም የመጨረሻውን 30 ደቂቃ መመልከት ትችላላችሁ፡፡
ጨለማው የቤጅንግን ከተማን እንደልብ እንዳንጎበኝ ሊያደርገን ነው ብላችሁም አትስጉ፤ እዛ ከጥሗቱ 1:35 ነው፡፡ ፀሐይ ወጣለች፡፡
ቻይና ቶሎ ነው የሚነጋው አይደል?
መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን በመመኘት!መረጃው ጠቃሚ ሆኖ አገኙት? እንግዲያውስ በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
ab sat dishPosts : 6
Points : 7
Reputation : 1
Join date : 2015-07-23
Age : 23
Location : Kolfe .tero &.Atenatera

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyFri Aug 21, 2015 1:19 pm

What about live channels
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyFri Aug 21, 2015 3:32 pm

ውድድሩ በአገርዉስጥ ቻናሎች ይተላለፋል ተብሎ ይገመታል፡፡
በAD sport ባደር እና ናይል ላይ በFTA እንዲሁም በEurosport ዩቴልሳት@7E ላይ ውድድሩ ከሚተላለፍባቸው ቻናሎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ውድድሩን ከFTA ሳታላይት ቻናሎች በተጨማሪ በIAAF ኦፊሻል የYouTube ቻናል ጭምር LIVE መከታተል ይቻላል፡፡በ3ጂ ግን እንዳይሞክሩት፤በዋየርድ ብሮድባንድ ብቻ፡፡


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
PrinceHairePosts : 4
Points : 4
Reputation : 0
Join date : 2015-08-19

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyFri Aug 21, 2015 11:54 pm

Bein sport 1 and 2 signal has down. Anybody any thought how i might gain control again on supermax SM9200 CA HD
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyFri Aug 21, 2015 11:57 pm

PrinceHaire wrote:
Bein sport 1 and 2 signal has down. Anybody any thought how i might gain control again on supermax SM9200 CA HD
ለጥያቄህ መልስ ባይሆንም [You must be registered and logged in to see this link.]
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySat Aug 22, 2015 8:09 am


ኢትዮጵያ በማራቶን ሁለተኛ፤ ሰባተኛ እና አስራአምስተኛ ሆና ዉድድሩን ጨርሳለች።
የኤርትራው አትሌት ግርማይ ገብረስላሴ 2፡12፤28 በሆነ ሰአት ወርቅ ሲያገኝ፤
የማነ በአርባ ሰከንድ ልዩነት ተከትሎት ገብቷል፡፡
የዩጋንዳው ሙታይ ደግሞ ሶስተኛ ሆኖ ዉድደሩን አጠናቋል፡፡

ውድድሩን ከጀመሩት ስልሳስምንት አትሌቶች ውስጥ አርባ ሁለቱ ውድድርን መጨረስ ሲችሉ፤
ሃያስድስቱ ግን ሳይጨርሱ አቆርጠዋል፡፡
ውድድሩን ከጨረሱት ውስጥ የታንዛኒያው ፋቢያኖ ጆሴፍ በ2፡35:27 በአርባሁለተኛነት ሲገባ ለራሱ
የአመቱን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ ጭምር ነበር፡፡
አንድ የኬኒያ አትሌት ሃያሁለተኛ በመሆን ሲጨርስ የተቀሩት ሁለቱ ግን አቅርጠው ወጠዋል፡፡
መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySat Aug 22, 2015 10:20 am

ዛሬ ከሰአት በኋላ በ9:50 ላይ የወንዶች 10,000m የፍፃሜ ዉድድር

ኢትዮጵያ በኢማነ መርጊያ፣ሙክታር እድሪስ እና ሞሲነት ገረመው ለውድድር ተዘጋጅታለች፡፡
በዚህ ዉድድር ላይ ከሚካፈሉ ሯጮች ሁሉ የአመቱ ምርጥ ሰአት ያለው፤ ለብሪታንያ የሚሮጠው ሞፋራህ ነው፡፡
ከተሰላፊዎቹ ዉስጥ ኬንያዊው ፖል ታንዋይ እና ሞፋራህ በዚህ አመት ከ27ደቂቃ በታች መግባት የቻሉ ብቸኛዎቹ ናቸው፡፡

አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ በዚህ ውድድር ተካፋይ ነው፡፡ በዝህ አመት ጥሩ የሚባል ሰአት አላስመዘገበም፡፡
ይልቅን ለካናዳ የሚሮጠው ካሜሮን ሌቪንስ በያዝነው አመት ጥሩ ሰአት ካስመዘገቡት ዉስጥ ተጠቃሽ ነው፡፡
ባህሬን አውቀ አያሌውን አሰልፋለች፡፡

እስካሁን በተደረገው ዉድድር(አንድ ብቻ ነው) የሜዳልያ ሰንጠረዡን የአፍሪካ ሃገራት ከአንድ እስከ ሶስት ይዘዉታል፡፡
ኤርትራ፤ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ በመከታተል፡፡
ይህ የደረጃ ሰንጠረዥ የወንዶች አስርሺ ፍፃሜ እስከሚደረግ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
መልካም እድልን እንመኛለን!


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ አገኙት? እንግዲያውስ በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySun Aug 23, 2015 2:15 am

የሜዳልያ ሰንጠረዥ
ERITREA ..............1ወርቅ
GREAT BRITAIN & N.I...1ወርቅ
GERMANY...............1ወርቅ
KENYA.................1ብር+1ነሐስ
PR OF CHINA1..........1ብር
ETHIOPIA..............1ብር
UGANDA................1ነሐስ
UNITED STATES.........1ነሐስመረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyTue Aug 25, 2015 10:24 am

እስካሁን ባለው ሂደት ጎረቤት አገር ኬኒያ በ 2ወርቅ፤2ብር እና 2ነሃስ የደረጃ ሰንጠረዡን በአንደኝነት ትመራለች፡፡
እኛም ብሩ ካለ ወርቁ ከገቢያ ብለን በ 2ብር ከአስትናጋጇ ቻይና ጋር በ11ኛ ደርጃ ላይ እንገኛለን፡፡
እስካሁን 19አገሮች መዳሊያ ማግኘት ችለዋል፡፡

የወንዶች 800ሜትር ፍጻሜ ዛሬ ከቀኑ 9:55 ላይ ይደረጋል
ኬኒያውያኖቹ በዚህም ሌላ ወርቅ አምጥተው መሪነታችውን አጠናክረው እንደሚይዙት ባለሙሉ ተስፋናቸው፡፡
ባይታገድ ኖሮ መሃመድ አማን ይህን ተስፋቸውን ፉርሽ ሊያደርገው ይችላል ተብለው ከሚጠበቁት አትሌቶች ዉስጥ ነበር፡፡


የሴቶች 1500ሜትር ፍፃሜ ዛሬ ከቀኑ 9:35 ላይ ይደረጋል
የቀድሞ ሻምፒዮና የስዊድን አትሌት አበባ አረጋዊ የምትሳተፍበትን ይህን ዉድድር ከኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ ላይ
እንዲህ በቀላሉ የሚወስድ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ኬኒያውያኑ ግን በFaith Chepngetich Kipyegon
አሁንም ሌላ ፈተና ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይፈራል፡፡

ለአትሌቶቻችን መልካሙን ሁሉ በመመኘት!
መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyTue Aug 25, 2015 4:18 pm

ኬኒያውያኖቹ የ400 መሰናክልና የ800ሜትር ወርቀን ወስደዋል፡፡ መሪነታቸውንም ይበልጥ አጠናክረውታል፡፡
ገንዘቤም እንደተገመተው 1500ን አላስቀምስ ብላለች፡፡የመጀመርያውን ወርቅ ላገሯ በማስገኘት።


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyWed Aug 26, 2015 12:08 pm

እስካሁን አስራስምንት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል
ከተበረከቱት አስራስምንት የወርቅ ሜዳሊያ ዉስጥ ኬኒያ፣ ብሪታኒያ እና ጀማይካ፤ አራት ሶስት ሁለት በድምሩ
ዘጥኝ ወርቅ በማግኘት የወርቅ ሜዳልያውን ሃምሳ ፐርሰንት በእጃቸው አስገብተዋል፡፡

የዉድሩ መሪ ኬኒያ እስካሁን ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡ አራት የዋርቅ፣ ሶስት የብር እና ሁለት የነሀስ፡፡
ኢትዮጵያ በአንድ ወርቅና ሁለት ነሃስ ደረጃዋን ወደ አምስት ከፍ አድርጋለች፡፡

እስከአሁን ሃያአምስት አገራት ሜዳልያ ማግኘት ችለዋል፡፡
ዛሬ እኛ የምንካፈልበት የፍፃሜ ዉድድር አይኖርም ኬኒያውያን ሴቶች ግን
ሶስት ሺ መሰናክል ፍፃሜን በጉጉት ይጠባበቅሉ፡፡ ለአፍሪካውያኑ መልካም እድል እንመኛለን፡፡

የወንዶች የአምስትሺሜትር ማጣርያን ሁሉም ኢትዮጵያውያን አልፈዋል፡፡
ዮሚፍ ቀጀልቻ ሞፋራህን አስከትሎ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፤ ሓጎስ ገብረሕይወት እና ኢማነ መርጊያ ደግሞ
በሌላ ምድብ አንደኛና አምስተኛ በመሆነ ለፍፃሜ አልፈዋል፡፡
ሞፋራህ የነበረበት እና ዮሚፍ በአሸናፊነት ያጠናቀቀበት ምድብ ፈጣን ሰአት የተመዘገበበት ሲሆን
የገቡበት ሰአት ከመጀመሪያው ምድብ ከ25ሰከንድ በላይ የተሻለ ነበር፡፡
የዚህ ዉድድር ፍፃሜ ቅዳሜ በ ስምንት ሰአት ተኩል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyWed Aug 26, 2015 4:58 pm

ኬኒያ በስድስት ወርቅ አንደኝነቷን አጠናክራለች
የኋላ ኋላ አንደኝነቷን ለሃያላኑ አገራት አሳልፋ ትሰጣለች ተብሎ ቢገመትም
ኬኒያውያኑ ግን አንደኛ ሆኖ ለመጨረስ ቆርጠው መነሳታቸውን አሳይተዋል፡፡
ከትራክ ዉድድር አልፈው የፊልድ ዉድድርንም ወርቅ ወደራሳቸው ካዝና መክተት ጀምረዋል፡፡

የጦር ዉርወራን በወንዶች ወርቅ ወስደዋል፡፡ የሚጠብቁትን ሌላ ወርቅም በትራክ ዉድድር በሴቶች
ሶስት ሺ መሰናክል አግኝተዋል፡፡ ብሪታንያ በሶስት ወርቅ ሁለተኛ ናት፡፡ ዩናይተድ ስቴትስ እና ጀርመን አሁንም
አንድ ወርቅ ብቻ ነው ያላቸው፡፡

አዝጋጁዋ ቻይና ወርቅ ነጥፎባታል፤ ሁለት ብር እና ነሃስ ነው እስካሁን ያገኘችው፡፡
አሁን ኬኒይያዊያኖቹ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱት የአጭር እርቀት ተወርዋሪዎቹ ጀማይካዊያን እና
ሶስት ወርቅ ያላት ብሪታንያ ናት፡፡ ሆኖም ኬኒያ ዙሩን የምር አክርራዋለች፡፡

ለአፍሪካ አዲስ ሪከርድ ይዛም ልትጨርስ ነው፡፡ ካሁን በኋላ በቀሪዎቹ የሴቶች እና የወንዶች 5ሺን ካልጨመሩ፤
እስካሁን ኬኒያውያን ከኛ ላይ የወስዱት የሴቶችን የ10ሺ ሜትር ወርቅ ብቻ ነው፡፡
ጎረቤት ኬኒያን እያስመዘገበች ባለችው ዉጤት እንኩዋን ደስ አለሽ ማለት እንወዳለን፡፡


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptyThu Aug 27, 2015 9:13 am

የዛሬዉን የቤጂንግ ዉድድር በዩቴልሳት@7.0°E ፊድቻናል 11080 H 9874(24 0C 95 C5 4F EC 63 9E) ላይ መከታተል ይቻላል፡፡


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySat Aug 29, 2015 12:55 am

የውንዶች አምስት ሺ የፍፃሜ ዉድድር ዛሬ በ 8:30
ኢትዮጵያ በ ሶስት አትሌቶች ትወከላለች ፡-

  • Yomif Kejelcha
  • Hagos Gebrhiwet
  • Imane Merga

Mo Farah ትልቅ ግምት ተሰጦታል፡፡ ኬኒያም እንደኛው በሶስት አትሌቶች ትወከላለች፡፡

USA ወርቋን አራት አድርሳለች፡፡ በሴቶችም በወንዶችም አራት በመቶና አራት በአራት መቶ የዱላ ቅብብል
ዉድድሮች ላይእንደምታይል ከወዲሁ ተገምቷል፡፡ እናም ኬኒያ አንደኝነትዋን አስጠብቃ ለመጨረስ ዛሬ
የሚደረገውን የወንዶችስምንት መቶ ሜትር ፍጻሜ ዉድድር በጉጉት ትጠብቃለች፡፡

መልካም እድል!


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySat Aug 29, 2015 3:50 pm

ሞ ፋራህ ወርቁን በድጋሚ በ አምስትሺም ወስዷል። ኬኒያና ኢትዮጵያ ሁለትኛና ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡
USA አምስተኛ ወርቋን አግኝታለች፡፡ አንደኛ ሆና መጨረሷም አይቀሬ እየሆነ ነው፡፡
የሴቶች ስምንት መቶ ሜትሩን ኬኒያ አልቀናትም፤ ሶስተኛ ሆና ነው የጨረሰችው፡፡
አሁን ለኬኒያም ሆነ ለኢትዮጵያ የሚጠበቀው የነገው የሴቶች አምስትሺ እና ማራቶን ነው፡፡
የወንዶች ሺአምስትመቶም ነገ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySat Aug 29, 2015 6:45 pm

ወቅታዊው የሜዳሊያ ሠንጠረዥ
ደረጃሀገርወርቅብርነሐስድምር


1ኬኒያ64313


2ጀማይካ62311


3አሜሪካ55616


4ብሪታኒያ4105


5ፖላንድ3148


6ሩሲያ2114


7ኪዩባ2103


8ቻይና1517


9aካናዳ1337


9bጀርመን1337


11ኢትዮጵያ ሀገራችን1214


ጀማይካዎቹ በዱላ ቅብብል በወንዶቹም በሴቶቹም 4x100ን እየተወረወሩ ወርቁን ወስደዉታል፡፡
የመቶ ሜትሮቹ ባለወርቅ ሁሴን ቦልት እና ፍሬይዘር ፕሪስ ዱላዉን ይዘው ሌላ ወርቅ በጋራ አምጥተዋል፡፡
አሁን ጀማይካም ከኬኒያ እኩል ስድስት ወርቅ አላት፡፡ አንዱን ወርቅ USA አግኝታው ቢሆነ ኖር መሪነቱን ትረከብ ነበር።
መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySun Aug 30, 2015 5:26 am

ማሬ ዲባባ በሴቶች ማራቶን አሸናፊ ሆናለች።
ለ ኢትዮጵያም ሁለተኛው ወርቅ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySun Aug 30, 2015 2:17 pm

Happening now 5,000m final
Back to top Go down
kstar
Senior member
kstar

Posts : 1052
Points : 2022
Reputation : 844
Join date : 2015-05-23

 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች EmptySun Aug 30, 2015 7:23 pm

ዛሬ የቤጅንግ የአለም ሻምፒዮና ፍጻሜ አግኝቷል
የሜዳሊያ ሠንጠረዡም እንደሚከተለው ነው

ደረጃ----ሀገር--------------ወርቅ---------ብር----------ነሐስ----------ድምር---------


1ኬኒያ76316


2ጀማይካ72312


3አሜሪካ66618


4ብሪታኒያ4127


5ኢትዮጵያ 3328


6ፖላንድ3148


7aካናዳ2338


7bጀርመን2338


9ሩሲያ2114


10ኪዩባ2103


11ቻይና1719


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡
Back to top Go down
Sponsored content
 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty
PostSubject: Re: የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች    የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች Empty

Back to top Go down
 
የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች
Back to top 
Page 1 of 1

Permissions in this forum:You cannot reply to topics in this forum
የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ :: አጠቃላይ ኢንፎርሜሽን: ሳተላይት ቲቪ :: የየቀኑ የሳተላይት ቲቪ ዜና :: የዛሬ ኳስ ግጥሚያ ፕሮግራም-
Jump to: