የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ
ለውድ የፎረሙ አባሎች በሙሉ:-- ፎረሙን እንደምታዩት የተለያየ ማሻሻያዎች እያረግንበት ነው:: ይጨመር ይቀነስ የምትሉት ነገር ካለም: ለማስተካከል ዝግጁ ነን:: ጥያቄአችሁን ወይም ፓስት የምታደርጉትን ነገሮች በተሰጡት የካታጎሪ ምድቦች ውስጥ: እንደአይነቱ በአይነቱ እንድታስቀምጡ እያስታወቅን: Log in በማረግ ይጠቀሙ::
እናመሰግናለን፡፡ አድሚኖች::


ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስ እንሞክራለን:: በዚህ ፎረም ተረዳድተን ስለዲሽ: ሳተላይት ሪሲቨር: እንዲሁም ሪሲቨር ሶፍትዌሮች እንወያያለን::
 
HomeHome  CalendarCalendar  GalleryGallery  SearchSearch  RegisterRegister  Log in  

እንኩዋን ደህና መጡ
Who is online?
In total there are 4 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 4 Guests

None

Most users ever online was 41 on Sat Jul 02, 2016 11:21 am
Most active topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
Installers Phone Numbers And Location ዲሽ አስተካካዮች ስልክና አድራሻ እዚህ ያስቀምጡ
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Loader for all Spermax receivers
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Most Viewed Topics
የSupermax ሪሲቨሮች አፕዴት ሶፍትዌሮች
የዲጂተርክ ሶፍትዌር አንዳንድ ሰዎች እየጠየቁን ስለሆነ ለሁሉም ሪሲቨር የሚሰራ እዚህ ፔጅ ገብታችሁ ዳውንሎድ አርጉ
የዛሬ ጨዋታዎች የሚተላለፉባችው ቻናሎች ዝርዝር + LIVE FEEDS
አዳዲስ በሶፍትዌር የተከፈቱ Azam Tv Package ኢንኪሪፕትድ ቻናልስ Eutelsat 7E
Solution For Idman Azerbaycan For Free!
Biss Procedure for all SuperMax Receiver Model
በEutelsat 7E 12521 H 27500 የሚገቡ BISS channels
procedure for Inserting Cryptoworks for supermax reciever ?
Loader for all Spermax receivers
Idman Azerbycan TV ልክ ኳስ በቀጥታ ሊተላለፍ ሲል ለምን ይጠፋል? መፍትሄስ አለው ወይ?
Top posting users this week

Share | 
 

 ፉት ፕሪንት (Foot print)

Go down 
AuthorMessage
Admin
Admin
avatar

Posts : 727
Points : 1176
Reputation : 304
Join date : 2014-09-01

PostSubject: ፉት ፕሪንት (Foot print)   Wed Jun 24, 2015 2:03 pm

ፉት ፕሪንት (Foot print)

ስለዲሽ ትንሽ መረዳት ያላቸው ሰዎች ብዙ ግዜ ስለፉት ፕሪንት ሲናገሩ እንሰማለን:: ምናልባት ብዙም መረዳት ለሌለን ሰዎች ትንሽ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያህል: ዛሬ ስለፉት ፕሪንት ትንሽ ዝርዝር መግለጫ ይዤ ቀርቢያለሁ::

አንድ የሳተላይት ቴሌቭዢን ካምፓኒ የተለያዩ ቻናሎችን ወደሚፈልጋቸው ቦታዎች ወደሰዎች ለማድረስ ሳተላይት ይጠቀማል:: እንግዲህ ከመሠረቱ ለማስረዳት ያህል ይህ የቴሌቭዢን ካምፓኒ ሊጠቀም የፈለገው ሳተላይት መጀመርያ ከመሬት ወደህዋ (ሰማይ) መላክ አለበት:: ይበልጥ ለማስረዳት ያህል ብዙዋቻችን የምናውቀውን አንድ ምሳሌ ልጠቀም....

ናይል ሳት መካከለኛው ምስራቅ: ሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢን ለመድረስ የተላከ ሳተላይት ነው:: በእዚህ ሳተላይት በመጠቀም: የተለያዩ ካምፓኒዎች በእዚህ አካባቢ ለሚኖረው ሕዝብ ያላቸውን የተለያዩ ፕሮግራማቻቸውን በተለያዩ ቻናሎቻቸው ያደርሳሉ:: እንግዲህ ወደእነዚህ ሕዝቦች ሁሌ ሳይቋረጥ ለመድረስ ናይ ሳት ተብላ የተጠራችው ሳተላይት ሳታቋርጥና ካለችበት ቦታ ሳትዛነፍ ከመሬት እየተቀበለች ማስተላለፍ አለባት::

ከመሬት የተቀበለችውን ሳትዛነፍ ለእነዚህ አካባቢዎች ሁሌ ለማድረስ ቦታዋን ሳትለቅ ባለችበት መቀጠል አለባት:: ሁላችንም እንደምናውቀው መሬት ቀጥ ያለች ሳትሆን በራስዋ ዛቢያ በፍጥነት የምትሽከረከር ናት:: ሳይንቲስቶች እንደሚነግሩን በሰከንድ 465 ሜትር በሰዓት ደግሞ 1675 ኪሎ ሜትር በራስዋ ዛቢያ ትሽከረከራለች:: እንግዲህ አስቡት: ይህቺ ሳተላይት (ናይል ሳት) ቦታዋን ሳትለቅ ባለችበት ለመቆየት እኩል ከመሬት ጋር አብራ መሽከርከር አለባት:: ይህንን ሁኔታ Geosynchronous orbit ይሉታል:: ይህቺ ሳተላይት እንዲህ በጥናት ተስተካክሎ ካልተላከች ትንሽም መዘግየት ወይም ትንሽም መፍጠን ካለ በቦታዋ ስለማትገኝ በትክክል ለታሰበችለት አላማ መዋል አትችልም: ሰዎችም ሳተላይት ቻናሎችን ማየት አይችሉም:: ስለዚህ በትክክል ምንም አይነት መዛነፍ ሳይኖር ሳተላይትዋ ከመሬት ፍጥነት ጋር እኩል ቦታዋን ሳትለቅ መሽከርከርዋ ለታሰበችለት አላማ እንድትውል ያደርጋታል::
እዚህ ድረስ ባለው ነገር ግንዛቤ ከጨበጥን ፉት ፕሪንት ወደሚለው እንግባ...

አሁንም ይበልጥ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የናይል ሳትን እንደምሳሌ እጠቀማለሁ:: ናይል ሳት ከመሬት ከተለያዩ ቴሌቭዢን ካምፓኒዎች የተቀበለችውን ፕሮግራሞች መልሳ ለታለመላቸው አካባቢዎች ለማድረስ የምትለቀው ሞገድ ወይም ሳተላይት ቢም የሚያርፍባቸው አካባቢዎች ፉት ፕሪንት ተብለው ይጠራሉ:: ለምሳሌ በማታ ባትሪ ግርግዳ ላይ ብናበራ የባትሪው ብርሃን በግድግዳው ላይ የሚያርፈው እኛ እንደቆምንበት ርቀት የተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ ነው:: ሳተላይቱም ወደመሬት የሚልከው ቢም የሚያርፈው የተወሰኑ አካባቢዎች ነው:: ወደመሐሉ አካባቢ ዋናው ቢሙ የሚያርፍበት ስለሆነ በጣም ጠንካራ ነው:: ከመሐሉ እየራቀ በመጣ ቁጥል ደግሞ ሐይሉ እየቀነሰ ይመጣል::
ዋናው ቢሙ የሚያርፍበት ቦታ ያሉ ሰዎች ይህንን የሳተላይት ቢም ለመቀበል ትንሽ ዲሽ ብቻ ሲያስፈልጋቸው: ከዋናው ቢም ራቅ ያሉ ቦታ የሚገኙ ደግሞ ከሳተላይቱ የሚላከውን ለመቀበል ትልቅ ዲሽ ያስፈልጋቸዋል::

ብዙ ጊዜ ስለዲሽ የተወሰነ እውቀት ያላቸው ሰዎች ስለአንድ ሳተላይት ላይ ስላለ ቻናሎች ዝርዝር በሚያዩበት ጊዜ EIRP (equivalent isotropically radiated power) አብረው ይመለከታሉ:: EIRP በመሬት ላይ የሳተላይቱ ሲግናል ጥንካሬ ተለክቶ የሚፃፍበት ነው:: ስለዚህ EIRP ከፍ ያለበት አካባቢ የሳተላይቱ ሲግናል ጥንካሬ ከፍ ያለበት ነው:: EIRP ዝቅ ያለበት ደግሞ ሲግናሉ ዝቅ ያለበት ነው:: ፉት ፕሪንቱን በመመልከት ለምሳሌ አዲስ አበባ ለሚኖር ሰው በትንሹ ሳህን ወይም በትልቁ ሳህን መጠቀም እንደሚችል መንገር ይቻላል:: ደግሞም ሳተላይቱ እኛ አካባቢ አይደርስም ወይም ይደርሳል ብሎ መናገር ይቻላል::

በሚቀጥለው ፅሁፌ ደግሞ እንዴት የቴሌቭዢን ካምፓኒዎች ፕሮግራሞቻቸውን በVideo Compression ተጠቀመው MPEG-2 ወይም MPEG-4 እንደሚልኩ የተወሰነ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እሞክራለሁ::


መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡


Last edited by kstar on Wed Aug 05, 2015 3:48 pm; edited 4 times in total (Reason for editing : navigation)
Back to top Go down
http://ethiodish.amharicforum.com
binihighPosts : 1
Points : 2
Reputation : 1
Join date : 2015-07-13

PostSubject: Re: ፉት ፕሪንት (Foot print)   Mon Jul 13, 2015 5:37 pm

good information thank you ;
Back to top Go down
tamiratta
Member


Posts : 92
Points : 133
Reputation : 37
Join date : 2014-10-03

PostSubject: Re: ፉት ፕሪንት (Foot print)   Tue Jul 14, 2015 9:02 am

Excellent info,thanks admin.
Back to top Go down
AB
Junior member


Posts : 11
Points : 19
Reputation : 0
Join date : 2015-05-04
Age : 21

PostSubject: Re: ፉት ፕሪንት (Foot print)   Tue Jul 14, 2015 1:28 pm

The footprint of a
communications
satellite
is the ground area that
its transponders offer
coverage, and
determines the satellite
dish diameter required
to receive each
transponder's signal.
There is usually a
different map for each
transponder (or group
of transponders), as
each may be aimed to
cover different areas.
Footprint maps usually
show either the
estimated minimum
satellite dish diameter
required or the signal
strength in each area
measured in dBW.
Back to top Go down
EwnetuPosts : 8
Points : 9
Reputation : 1
Join date : 2015-02-26

PostSubject: Re: ፉት ፕሪንት (Foot print)   Wed Aug 05, 2015 11:09 am

Thank You

Ewnetu

Back to top Go down
Sponsored content
PostSubject: Re: ፉት ፕሪንት (Foot print)   

Back to top Go down
 
ፉት ፕሪንት (Foot print)
Back to top 
Page 1 of 1
 Similar topics
-
» The Bloody Footprint
» Ernest Alvia “Smokey” Smith VC: Seaforth Highlanders
» How justice and forensics are changing today
» Canada and the Charge of the Light Brigade
» S.A. DRAGO Constructions (Karl)

Permissions in this forum:You cannot reply to topics in this forum
የኢትዮጵያውያን ስለ ዲሽና ሪሲቨር መወያያ መድረክ :: Installation and Support :: General Discussions: Installation and Support-
Jump to: